Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Month: June 2025

CERPHI

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ hope SBH ከተባለ አጋር ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ ፡

በክልሉ በተፈጥሮ ከመጠን በላይ የፈሳሽ ክምችት እና የነርቭ ዘንግ ክፍተት ተጠቂ የሆኑ ህጻናት ህክምና እና ድጋፍ እንዲያገኙ የሚያስችል ስምምነት መሆኑ ተገልጿል ፡፡ ስምምነቱን በማስመልከት ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በክልሉ በተፈጥሮ የጤና ችግር ያለባቸው ህጻናት ፈጣን ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ በተለይም በተፈጥሮ የከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ…
Read more

ለሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት አዳዲስ የኢኖቬሽን ስራዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ – ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ

ለሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት አዳዲስ የኢኖቬሽን ስራዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ – ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ (ሆሳዕና፣ ሰኔ 20/2017)፦ በኢትዮጵያ ለሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት አዳዲስ የኢኖቬሽን ስራዎች ተግባራዊ እንደሚደረጉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ተናገሩ። “ኢኖቬሽን ለሁለንተናዊ የጤና ሽፋን” በሚል መሪ ሃሳብ ላለፉት ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሔድ የነበረው አለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽንና ጥራት ጉባኤ ተጠናቋል። የጤና…
Read more

የምግብ ደህንነትን በማረጋገጥ በአካልና በአእምሮ ላይ የሚያጋጥመንን የጤና እክል መከላከል ይገባል – ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ

(ሆሳዕና:- ሰኔ 20/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በክልሉ በሚገኙ የዱቄትና ዱቄት ውጤት አምራቾች ጋር በንጥረ ነገር የበለፀገ ምርት ማምረት የሚያስችል የምክክር መድረክ በቡታጅራ ከተማ እያካሄደ ነው። የማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ የምግብ ደህንነትን በማረጋገጥ በአካልና በአእምሮ ላይ የሚያጋጥመንን የጤና እክል…
Read more

ፈጠራን ባሕል በማድረግ የሕክምና ዘርፉን መደገፍ ይገባል

ፈጠራን ባሕል በማድረግ የሕክምና ዘርፉን መደገፍ ይገባል ሲሉ የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬሕይወት አበበ ገልጸዋል፡፡ ዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽን እና ጥራት ጉባኤ ዛሬ 2ኛ ቀኑን ይዟል። በጉባኤው ላይ “ፈጠራ ሁሌም ጥራትን ለማምጣት ይረዳል” ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ ፈጠራ የታከለበት ስራ የጤና ዘርፉን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል አመላክተዋል። በኢትዮጵያ የጤና ተደራሽነትና ጥራት ላይ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተው፤ ጥራት…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ የድጋፍ እና ክትትል ስምሪት ሰጠ ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ የድጋፍ እና ክትትል ስምሪት ሰጠ ፡፡ የ2017 የሁለተኛ ግማሽ ዓመት ማጠቃለያ ድጋፋዊ ክትትል ከ16/10/17 ዓ/ም ጀምሮ ከዞን እና ልዩ ወረዳ ጀምሮ እስከ እስከ ታች ጤና ተቋማት በመውረድ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት የድጋፍ ክትትል ስራ እንደሚሰራ በኦረንቴሽኑ ተገልጿል ፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ…
Read more

በክልሉ የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል ደህንነቱ የተጠበቀና አሰተማማኝ መረጃ ላይ የተመሰረተ ዉሳኔን ተጠቅሞ አዲስ ግኝት ለማዘጋጀት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።

የማዕ/ ኢት/ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የጥናት እና ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የመረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል በክልሉ ጤና ቢሮ የህብ/ ጤና ኢን/ት እንዲሁም ከዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ለተወጣጡ ባሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው ። በጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጥናት እና ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ስናፍቅሽ አየለ እንደተናገሩት የጤና መረጃ አስተዳደር…
Read more

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኤም ፖክስ (Mpox) በሽታ ቅድመ መከላከል ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን የክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ::

ኤም ፖክስ ወይም በተለምዶ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በመባል የሚታወቀው በከፍተኛ ፍጥነት ከሚሰራጩ በሽታዎች አንዱ መሆኑንና የአለም አቀፍ የጤና ስጋት ሆኖ የተመዘገበ በሽታ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ከደቡብ ሬዲዮ ቴሌቪዥን ድርጅት ጋር ባደረጉ ቆይታ ተናግረዋል። የኤም ፖክስ ቫይረስ የተገኘባቸው ግለሰቦች እንደ ሽፍታ፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ የንፍፊት ማበጥ፣ የቆዳ…
Read more

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የድንገተኛ ህክምና ቡድን (Emergency Medical Team – EMT) የተሟላ የመስክ ልምምድ (Full Scale Simulation Exercise) ተካሄደ::

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የድንገተኛ ህክምና ቡድን (Emergency Medical Team – EMT) የተሟላ የመስክ ልምምድ (Full Scale Simulation Exercise) ተካሄደ:: የብሔራዊ አደጋ ምላሽ አቅምን ለማጠናከር ትልቅ እርምጃ የሆነው የልምምድ መርሃግብሩ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) ከ UK MED እና UK Emergency Medical Team (UK EMT) ጋር በመተባበር በሀገሪቱ የመጀመሪያውን የተሟላ የድንገተኛ ህክምና የመስክ ልምምድ “የማይበገር የህብረተሰብ ጤና…
Read more

ወባን በመከላከል ረገድ የሚታየውን መዘናጋትና የትኩረት ማነስ ችግር በመቅረፍ በመጪው ክረምት ስፈላጊ እንደሆነ ተገልፀል፡፡

ወባን በመከላከል ረገድ የሚታየውን መዘናጋትና የትኩረት ማነስ ችግር በመቅረፍ በመጪው ክረምት ሊከሰት የሚችለውን የወባ ጫና ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ የክልሉ ጤና ቢሮ ጥሪ አቀረበ። ቢሮው ክልል አቀፍ የወባ መከላከል ስራዎችን በሀላባ ቁሊቶ እየገመገመ ነው። (ሆሳዕና፣ሰኔ 2/2017) ፣ ወባን በመከላከል ረገድ የሚታየውን መዘናጋትና የትኩረት ማነስ ችግር በመቅረፍ በመጪው ክረምት ሊከሰት የሚችለውን የወባ…
Read more

የዓለም ቆልማማ እግር ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ተከበረ ፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስቴርና Hope Walks ጋር በመተባበር የዓለም ቆልማማ እግር ቀንን በቡታጅራ በግራር ቤት የተሃድሶ ማዕከል ከታካሚ ህፃናትና ቤተሰቦቻቸው ጋር ተከበረ :: የዘንድሮ የአለም የቆልማማ እግር ቀን ” ወቅታዊ ፣ ውጤታማ ፣ ተደራሽ የዞረ እግር ህክምና ለሁሉም ህፃናት ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመሳሳይ ቀንና ጊዜ በሀዋሳ ከተማ የተከበረ ሲሆን በክልላችን…
Read more