Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Month: February 2025

በማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል ከየካቲት 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ በሆሣዕና ከተማ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል።

በማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል ከየካቲት 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ በሆሣዕና ከተማ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል። የከቲት 04/2017 ዓ.ም የማዕከላዊ ኢ/ክ/ጤ/ቢሮ የህ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ፖሊዮ (nOPV2) ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ ከዞንና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ጤና ባለሙያዎች በሆሳዕና ከተማ ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ሥልጠና መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ…
Read more

“ኢትዮጵያ ጠንካራና የማይበገር የጤና ስርዓት ለመዘርጋት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በቁርጠኝነት ትሰራለች።”

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮዽያ አባል የሆነችበት የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ 156ኛው ስብሰባ በስዊዝርላንድ ጀኔቫ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤን በማጎልበት፣ ጠንካራ የጤና ስርዓት እንዲኖር በቁርጠኝነት እየሰራች ትገኛለች ብለዋል። ሚኒስትሯ በማከልም ለዘላቂ የጤና መሰረት ስርአት፣ የሀገር ዉስጥ የህክምና ግብዓት ምርትን ለማሳደግ…
Read more

አመራሩ ሙሉ ትኩረቱን የህዝብ ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር አለበት – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

( ሆሳዕና፣ የካቲት 2/2017 )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር ) ከዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ዋና አስተዳዳሪዎች ጋር የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት አጠቃላይ ስራዎች አፈጻጸምን በጽህፈት ቤታቸው ገምግመዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር ) በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት አመራሩ ሙሉ ትኩረቱን የህዝብ ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር አለበት…
Read more

የሕብረተሰብ የጤና አደጋዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱና ፈተና እየሆኑ ስለመጡ የጤና ስርዓቱ ይህንን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት ሊኖረው ይገባል፡- የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ::

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት10ኛውን የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ፎረም ”የማይበገር የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ስርዓት ለብሄራዊ ጤና ደህንነት” በሚል መሪ ቃል በሃዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ ዛሬ እዚህ የደረስነው እንደሃገር በተለያዩ ጊዜያት ሲፈትኑን የነበሩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን በጋራ ምላሽ በመስጠት ነው፤ ለዚህ ደግሞ በየደረጃው የሚገኙ የጤናው…
Read more

የኮሌራ ወረርሽኝ ከተከስተ በኋላ የመልሶ ምልከታ ወርክ ሾፕ መስጠት መጀመሩ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የድንገተኛ ጤና አደጋዎችን ቅኝትና ምላሽ ከማጠናከር አኳያ እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል በርካታ ተግባራቶች እየተከናወነ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ገልጿል። በክልሉ ስር ከሚገኙ ዞንና ወረዳዎች ለተውጣጡ ድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ሰጪ ባለሙያዎች የሚሰጠው ስልጠና በዛሬው ዕለት በቡታጅራ ከተማ ተጀምሯል። የማ/ኢት/ክ/ጤ/ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ…
Read more

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ልማት ህብረት በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ላይ ያላቸዉን ተሳትፎ የሚያጠና የጥናት ስራ በተመለከተ በዛሬ ዕላት ለመረጃ ሰብሰቢዎች በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊሲ ጥናት ምርምር በጋራ በመሆን ” Level of Women Development Union Engagement on Health Extension programm at Central Ethiopia Region” በማእከላዊ ኢትዮጺያ ክልል የሴቶች ልማት ህብረት በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ላይ ያላቸዉን ተሳትፎ የሚያጠና የጥናት ስራ በተመለከተ በዛሬ ዕላት ለመረጃ ሰብሰቢዎች በሆሳዕና ጤና ሳይንስ…
Read more

የጤና ተቋማትን ለህክምና ዝግጁ ከማድረግ ባሻገር ለድንገተኛ የጤና አደጋዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ ማድረግ ይገባል።

የጤና ተቋማትን ለህክምና ዝግጁ ከማድረግ ባሻገር ለድንገተኛ የጤና አደጋዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጡና ወረርሽኝን መመከት የሚችሉ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በማህበረሰቡ ላይ የሚከሰቱ ድንገተኛ የጤና አደጋዎችን አስቀድሞ በመተንበይ በመተንተንና ፈጣን ምላሽ በመስጠት ማህበረሰቡን ከተለያዩ የጤና አደጋዎች መከላከል እንደሚገባ ጠቁመው በክልሉ ውስጥ 6 ሆስፒታሎች ላይ…
Read more

የሀዲያ ዞን የማዐጤመ አፈጻጸም የክልል ጤና ቢሮ አካላት ባሉበት ተገመገመ።26/5/2017

ከክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በአቶ ማሙሽ ሁሴን፣ ምክትል ኃላፊና የጤና ቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ አባይነህ ኤርቃሎን፣ ዳይሬክተሮችና ከፍተኛ ኤክስፔርቶቾ ጨምሮ የዞኑ የእስከአሁን ያለው የማዐጤመ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን በአፈጻጸም ግምገማ መነሻ ላይ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ደሣለኝ ሽጉጤ አጠቃላይ የዞኑን ነባራዊ ሁኔታ ከአፈጻጸሙ ጋር በስፋት አንስተዋል። በመቀጠልም በቀረበዉ ሪፖርት መነሻ ከክልል…
Read more

የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በማዕከላዊ ኢትዮጺያ ክልል በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች ከየካቲት 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ በቤት ለቤት ጉብኝት ይሰጣል!!

የፖሊዮ በሽታ በአገራችን ለብዙ ህጻናት ህመም፣ የአካል ጉዳትና ሞት ምክንያት ከሆኑት በሽታዎች መካከል አንዱ ነዉ። የፖሊዮን በሽታ መከላከል የሚቻለው ህጻናትን በመደበኛና በዘመቻ መልክ የሚሰጠውን ክትባት ስናስከትብ ነው!! በመሆኑም የመጀመሪያ ዙር የፖሊዮ ክትባት እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ከየካቲት 14-17/2017 ዓ.ም ድረስ በቤት ለቤት ጉብኝት ይሰጣል፡፡ስለሆነም ህፃናት ከዚህ ቀደም የፖሊዮ ክትባት ቢከተቡም ባይከተቡም በዘመቻው እንዲከተቡ…
Read more

በጤናው ዘርፍ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በሳይንሳዊ ምርምር በማስደገፍ የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመላከተ

(ሆሳዕና፣ጥር 24/2017 )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በባህላዊ መድሀኒት ጥናት ላይ በትብብር መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ውል ስምምነት ተፈራረሙ የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ እንደገለጹት ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የህዝቡን የጤና ችግሮች መፍታት የሚችሉበትን እድል መፍጠር ይገባል ብለዋል። በክልሉ ካሉ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ቅንጅት በመፍጠር በጤና…
Read more