Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Month: January 2025

Ato Samuel Darge and Ato Ashenafi Petros

የጤና ኤክስቴንሽኖች የተሃድሶ ስልጠና መስጠት መጀመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ።

የጤና ኤክስቴንሽኖች የተሃድሶ ስልጠና መስጠት መጀመሩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል። ከክልሉ ስልጤ፣ ጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ እና ሀላባ ዞኖች ከተመረጡ ወረዳዎች ለተውጣጡ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የሚሰጠው ስልጠና በዛሬው ዕለት በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል። የቢሮው ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት በክልሉ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ በመግለጽ በበጀት ዓመቱ ከታቀዱ ተግባራቶች አንዱ…
Read more

Ministry Of Health

የጤና ሚስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌይኒ ተርኪኺን የተመራ ልዑካን ጋር በጤናው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

የጤና ሚስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌይኒ ተርኪኺን የተመራ ልዑካን ጋር በጤናው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ ____________ የጤና ሚስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌይኒ ተርኪኺን የተመራ ልዑካን ጋር በጤናው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ እና ራሺያ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸው ትብብር በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ ወዳጅ…
Read more

የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ የድጋፋዊ ክትትል ግብረ መልስ ሪፖርት አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።

በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አስሩም መዋቅሮች የተሰማራው የድጋፋዊ ክትትል ቡድን ግብረ መልስ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። የውይይት መድረኩን የመሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የድጋፍ ክትትል ቡድኑ አባላት በድጋፍ ክትትሉ ወቅት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡና በቁርጠኝነት ለመወጣት ላዳረጉት ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዋል። በድጋፍ ክትትሉ በጉድለት ለተለዩ ጉዳዮች የአጭርና የረዥም ጊዜ የድርጊት መርሃ ግብር በማውጣት…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል EOC ሳምንታዊ ግምገማ አካሂዷል።

ጥር 20/2017 ዓ/ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል EOC ሳምንታዊ ግምገማ አካሂዷል። የቢሮው ጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ከለላው አቻምየለህ የሳምንቱን ሪፖርት ሲያቀርቡ ባለፈው ሳምንት የነበረው የወባ ጫና በዚህ ሳምንት 2.1% ጭማሪ አሳይተዋል ብሏል። ባለፈው ሳምንት 6685 የነበረው በዚህ ሳምንት…
Read more

ጥራቱን የጠበቀ የምጥና የወሊድ አገልግሎት በመስጠት በእናቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ሞት ለማስቀረት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተመላከተ

ጥራቱን የጠበቀ የምጥና የወሊድ አገልግሎት በመስጠት በእናቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ሞት ለማስቀረት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተመላከተ (ጥር19/2017 )በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጤናማ እናትነት ወር ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እንደገለጹት የጤናማ እናትነት ወር መከበር አብይ ዓላማ የእናቶችንና የህፃናትን ጤና በማሻሻል ጤናማ ህብረተሰብን ለመፍጠር ያለመ…
Read more

ወባን ለማስወገድ አዳዲስ ስልቶች እና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም በሚቻልበት መንገድ ላይ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት ተካሄደ

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በመድረኩ እንደተናገሩት ስብሰባው የወባ መድሃኒቶችን ወጪ ለመቀነስ እና ወባን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማጎልበት የሚስችሉ ስልቶች ላይ ለመወያየት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል። የወባ በሽታን ለመከላከል የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ አስፈላጊነት እና ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ዶ/ር መቅደስ የተናገሩ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ ተቋሞችን ማጠናከር እና የመከላከል ስራዎችን ማጎልበት ከጥረታቸው ግንባር ቀደም መሆን እንዳለበት…
Read more

Metheorology

በቀጣይ 10 ቀናት የሚኖረውን የበጋ ደረቅ ርጥበት በመጠቀም ምርት መሰብሰብ ይገባል- ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

በሚቀጥሉት 10 ቀናት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል የሚኖረውን የበጋ ደረቅ ርጥበት በመጠቀም አርሶ አደሮች ሰብል የመውቃትና ምርት የማጓጓዝ ስራ እንዲያከናውኑ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ። ኢንስቲትዩት ለኢዜአ በላከው የትንብያ መግለጫ እንደጠቆመው በቀጣይ 10 ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ፀባይ ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በሰሜን፣ በምሥራቅ፣ በሰሜን ምሥራቅና በደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሌሊትና በማለዳ ቅዝቃዜ እንደሚኖር…
Read more

የአፍሪካ ህብረት አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት የመውጣቷን ውሳኔ እንድታጤነው ጠየቀ::

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት የመውጣቷን ውሳኔ መልሳ እንድታጤነው ጠይቀዋል፡፡ ሙሳ ፋኪ አሜሪካ ከድርጅቱ አባልነት ለመውጣት መፈለጓ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፤ ውሳኔውን መለስ ብሎ በማጤን በአባልነቷ ትቀጥላለች የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። የአፍሪካ ህብረት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ አሜሪካ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) መስረታ ላይ ቀደምት እና…
Read more

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በወቅታዊ ተግባራት ላይ ውይይት ማድረጉን ገለፀ

ጥር 14/2017 የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በወቅታዊ ተግባራት ላይ ውይይት ማድረጉን ገለፀ በክልሉ በዚህ አመት የተከናወኑ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች እና ወረርሽኞች ቁጥጥር ላይ ከፍተኛ መሻሻል የታየበት እና ይህም ተግባሩ በቅንጅት በመመራቱ የተነሳ የመጣ ውጤት ሲሆን በተለይ ከክትባት ጥራት እና ተደራሽነት እንዲሁም ክትባት ያልወሰዱ እና ያቋረጡ ህፃናትን ለይቶ የመከተብ ስራ (Big-Catch Up Campaign) በሁሉም…
Read more

ጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ከአራት ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ አገኘ::

ጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ከአራት ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ አገኘ ____ አሲስት ኢንተርናሽናል የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ወደ ሁለት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ዘጠና አራት ሺ ሶስት መቶ ዶላር እና ሪች አናዘር ፋውንዴሽን ደግሞ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ የህክምና መሳሪዎችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ የተሻሻለው የጤና ፖሊሲ በሽታን…
Read more