Central Ethiopia,Worabe
cerphi@cerphi.gov.et

Month: November 2024

የወባ በሽታ የሚያሳድረውን ሁለንተናዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ ባለድርሻ አካላት ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥተው ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ገለፁ!

ዋና አስተዳዳሪው ይህን ያሉት የዞኑ ጤና መምሪያ የወባ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ የንቅናቄ መድረክ በወራቤ ከተማ እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው ሲል ስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቦታል።

ከደቡብ እና ማዕከላዊ ኢትዮዽያ መሠረታዊ የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ስልጠና ያጠናቀቁ ባለሙያዎች ሰርተፍኬት ተቀበሉ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል የዝግጁነት ዳይሬክቶሬት ከኢንስቲትዩቱ ብሔራዊ የስልጠና ማዕከል ጋር በመተባበር ከደቡብ እና ማዕከላዊ ኢትዮዽያ ተውጣጥተው በሶስት ዙር የተሰጠውን መሰረታዊ የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ስልጠና (Frontline-FETP) ያጠናቀቁ 27 የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ባለሙያዎች ዛሬ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ አስመረቀ፡፡ አቶ አወል ዳውድ የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ባለሙያ እና…
Read more

የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ሣምንታዊ የEOC ግምገማ አካሂዷል

የወባ በሽታ ስርጭትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር እንዲቻል ለማድረግ ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ማህበረሰቡ ድረስ የመከላከልና የቁጥጥር ሥራ ላይ በንቃት ማሳተፍ እንደሚገባ ተገልጿል። የወባ በሽታ በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖና ጫና ለመከላከልና ለመቆጣጠር በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉት ርብርብ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተመላክቷል ። የወባ መከላከል ተግባራትን ለማጠናከር በወረዳዎች የተሰራ በድጋፍና ክትትል የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ…
Read more

ጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጥናት ለሚያደርግ የጥናት ቡድን ስምሪት መሰጠቱ ተገለጸ።

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ለጥናታዊ ቡድኑ የስራ ስምሪት በሰጡበት ወቅት ጥናቱ በክልሉ ባሉ ሁሉም መዋቅሮች በ39 ጤና ጣቢያዎች በ10 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች እና በ3 አጠቃላይ ሆስፒታሎች በጥናት የተደገፈ ተግባር የሚፈጽም መሆኑን አስረድተዋል። የሰው ሀይል ውጤታማነት፣ የግብአት እና የመድሀኒት አቅርቦት እንዲሁም አስተዳደርን፣ የፋይናንስ ስርአት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እንዲሁም በጤና ተቋማት የሚታዪ…
Read more